Posts

Showing posts from January, 2024

ገናን (ክሪስማስን) Christmas ማክበር አስፈሪ ነው!እውነቱ ምንድን ነው!

Image
  በአለም ዙሪያ ያሉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ   ክርስቲያኖች ቀኑን በጉጉት በመጠበቅ ፣እርስ በርሳችሁ ስጦታ በመለዋወጥት ቀኑን ቅዱስ እንደሆነ በማሰብ የሚያከብሩት በአል ነው ገና፡፡ እውነታው ግን   የገና በዓል   ከየሱስ ክርስቶስ ልደት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ብላችሁስ፡፡ የገና በአል ከክርስቶስ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው እና   ወደ ክርስትና እምነት እንዲገባ በዘመናት ውስጥ የተደረገ ውሸት እንደሆነ ብነግራችሁስ፡፡ ታህሳስ 25 በጥንት ሮማውያንና ባቢሎናውያን የአምልኮ ስርአት የሚካሄድበትና ገናም ሴይጣናው አምልኮ ነው ብላችሁስ፡፡ በዚህች አጭር ጽሁፍ ጨለማውን በመግለጥ ስለ ገና ጥቂት እውነት እነግራችኋለሁ፡፡ አንደው ለመሆኑ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የገና ዛፍ ፤ የገና አባት፤ ስጦታ ተብሎ የሚዘጋጁ የተለያዩ ስጦታዎች፣ቁሳቁሶች ፣ጭፈራ ፣በግ ማረድ ፣.ሌሎችም ነገሮች ከክርስቶስ ልደት ጋር ምን ያገናኛቸዋል? ይሄን የሚጠይቅ አለ? እውነት የክርስቶስ ልደት ታህሳስ ወር እንደሆነ ማን ነው ያረጋገጠው ።መጽሀፍ ቅዱስ ላይ አንድም ቦታ ክርስቶስ   የተወለደው ታህሳስ ወር ነው አይልም፡፡ ክርስቶስ የተወለደበትን ቀን ማንም በእርግጠኘነት ሊናገር አይችልም፡፡ ምክንያቱም እውነታው ሌላ ስለሆነ፡፡  እስከ 16ኟው ክፍለ ዘመን በአብዛኞቹ የአሜሪካን ግዛቶች የገና በአል እንዳይከበር የተከለከለ ነበር   1647 በእንግሊዝ ፓርላማ የገና በአል እንዳይከበር የተከለከለ እና የሚያስቀጣ እንደነበር ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡ ታዲያ የክርስቶስ የልደት በአል ነው ብሎ በታህሳስ ወር ማክበር ከየት የመጣ ነው? እውነታውስ ምንድን ነው? ለምንስ እውነቱን   ሊደብቁን ፈለጉ? ለዘመናትስ ሲያስ...