ገናን (ክሪስማስን) Christmas ማክበር አስፈሪ ነው!እውነቱ ምንድን ነው!

 





በአለም ዙሪያ ያሉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ  ክርስቲያኖች ቀኑን በጉጉት በመጠበቅ ፣እርስ በርሳችሁ ስጦታ በመለዋወጥት ቀኑን ቅዱስ እንደሆነ በማሰብ የሚያከብሩት በአል ነው ገና፡፡

እውነታው ግን  የገና በዓል  ከየሱስ ክርስቶስ ልደት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ብላችሁስ፡፡ የገና በአል ከክርስቶስ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው እና  ወደ ክርስትና እምነት እንዲገባ በዘመናት ውስጥ የተደረገ ውሸት እንደሆነ ብነግራችሁስ፡፡ ታህሳስ 25 በጥንት ሮማውያንና ባቢሎናውያን የአምልኮ ስርአት የሚካሄድበትና ገናም ሴይጣናው አምልኮ ነው ብላችሁስ፡፡ በዚህች አጭር ጽሁፍ ጨለማውን በመግለጥ ስለ ገና ጥቂት እውነት እነግራችኋለሁ፡፡



አንደው ለመሆኑ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የገና ዛፍ ፤ የገና አባት፤ ስጦታ ተብሎ የሚዘጋጁ የተለያዩ ስጦታዎች፣ቁሳቁሶች ፣ጭፈራ ፣በግ ማረድ ፣.ሌሎችም ነገሮች ከክርስቶስ ልደት ጋር ምን ያገናኛቸዋል? ይሄን የሚጠይቅ አለ? እውነት የክርስቶስ ልደት ታህሳስ ወር እንደሆነ ማን ነው ያረጋገጠው ።መጽሀፍ ቅዱስ ላይ አንድም ቦታ ክርስቶስ  የተወለደው ታህሳስ ወር ነው አይልም፡፡ ክርስቶስ የተወለደበትን ቀን ማንም በእርግጠኘነት ሊናገር አይችልም፡፡ ምክንያቱም እውነታው ሌላ ስለሆነ፡፡ 


እስከ 16ኟው ክፍለ ዘመን በአብዛኞቹ የአሜሪካን ግዛቶች የገና በአል እንዳይከበር የተከለከለ ነበር 1647 በእንግሊዝ ፓርላማ የገና በአል እንዳይከበር የተከለከለ እና የሚያስቀጣ እንደነበር ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡

ታዲያ የክርስቶስ የልደት በአል ነው ብሎ በታህሳስ ወር ማክበር ከየት የመጣ ነው? እውነታውስ ምንድን ነው? ለምንስ እውነቱን  ሊደብቁን ፈለጉ? ለዘመናትስ ሲያስመልኩን እና ሲዋሹን የነበረው እውነታ ምንድን ነው? እውነታው የሁሉም ነገር ምንጭ የሆነውን እውነተኟውን ፈጧሪ ሳይሆን የዚህን አለም ገዠ የሆነውን ከባቢሎን ጀምሮ በሮም በቫቲካን በአለም ባሉ ሀይማኖቶች ውስጥ እተመለከ ያለውን ሳተርንን ለማስመለክ እንደሆነ ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡



የገና በአል ጥንት ሮማውያን ልክ ክርስቶስ ተወልዶበታል በሚባለው በታህሳስ ወር ላይ የዚህ አለም ገዥ የሆነውን ሳተርንን የሚያከብሩበት ሳተርናሊያ የሚባል በአል አላቸው ፡፡የጥንት ሮማውያን ልክ ታህሳስ 12 ጀምረው እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ስራዎቻቸውን በማቆም ዛፎችን በማስጌጠ ስጦታ በመለዋወጥ ፤ ቅጥ ያጣ ወሲብ በየመንገዱ በመፈጸም፤ በስካር ፤የእንሰሳትን ደም በማፍሰስ የእርሻ የብልጽግበና አምላክ ለሚሉት ለሳተርን የሚገብሩበት ግዜ ነው፡፡ እንዲያውም በጥንት እስካንዲኔቪያን አገሮች የመዋለድ አምላክ ለሚሉት ልክ በገና በአል አካባቢ የሰው ደም ሁሉ ይገብሩ ነበር፡፡ እውነታው የገና በአል በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ በተለይ ሮማውያን የጸሀይን መወለድ እነሱ የጸሀይ አምላክ የሚሉትን የሚያከብሩበት በአል ነው፡፡







ከጥንት ግዜ ጀምሮ ታሪከ መጻፍ ከተጀመረበት ከ10ሺ አመት በፊት ጀምሮ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ጸሀይ ልዩ ቦታ ነበራት ለዚህ ምክኒያቱ የጥንት ሰዎች ጸሀይ የምትሰጣቸውን ጥቅም ያለጸሀይ በምድሪቱ ላይ ህይወት እንደማይኖር አጥብቀው ስለሚረዱ ነው፡፡ ጸሀይ በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ከ170 ግዜ በላይ ተጠቅሳለች፡፡ይሄ ምክኒያት ጸሀይን እጅግ አስፈላጊና የአምልኮ ምሳሌ እንድትሆን አስችሏታል፡፡ የጥንቶቹ ሰዎች ጸሀይንና የክዋክብት ስርዓቱ ከሰው ልጅ ጋር የሚያገናኛቸው አንዳች ሚስጠር እንዳለ ስለሚያውቁ በክዋክብት ጥናት የረቀቁ ነበሩ፡፡ ይሄ እውቀታቸው አሁን በኛ ዘመን አስትሮሎጂ፤ የክዋክብት ጥናት በአገራችንም ፤ባህረ ሀሳብ አቡሻህር እና አውደ ነገስትን የመሰሉ ጥንታዊ የክዋክብት ትምህርቶችን እናገኛለን፡፡




ታዲያ በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ አካባቢ የሚገኙ ሀገሮች ከባድ የሚባለው የክረምት ወራት አልፎ ወደ ጸደይ የጸሀይ ወራት  የሚገቡበት ወር ታሀሳስ 25 አካባበ የሚጀመር ስለሆነ ከጥንት ጀመሮ ጨለማውን እና ከባዱን የክረምት ወር ልክ እንደ ክፉና ሰይጣን በመመሰል የሚመጣውን የጸደይ ወር እንደ ብርሀን እና ጥሩ መንፈስ በመመሰል ከዚህም አልፈው ለነዚህ ወቅቶች አማልክት በመወከል ሲያከብሩት ነበር፡፡ የክዋክብትን ሚስጥራዊ አካሄድና ትርጉማቸውን በተፈጥሮ ላይ ያላቸውን ተጽእኖ ስለሚያውቁ በጥንት ዘመን የነበሩ የአማልክት ታሪኮች ከክዋክብት ጋር የተገናኙ የነበሩት፡፡ ከክስቶስ ልደት የቀደሙ ከድንግል የተወለዱ ብዙ የአማልክትን ታሪኮችን የምናገኘውም ለዚህ ነው ፤አብዛኞቹ ልክ እንደ ክርስቶስ ታህሳስ 25 የተወለዱ ፤ውልደታቸው ቀድሞ በነበያት የተነገረላቸው፤ልክ እንደ ክርስቶስ ከምስራቅ የሚመጡ ጥበበኞች በኮከብ ተመርተው እነሱ ጋር እንደሄዱ ፤በልጅነታቸው በአገራቸው ንጉስ የሚሳደዱ እንደነበሩ፤ ረጅም ግዜ በጾም የቆዩ፤አብዛኞቹ ልክ እንደየሱስ ታምር የሚሰሩ፤በውሀ ላይ የሚራመዱ ሙት የሚያስነሱ፤ አብዛኞቹ ለአለም ሀጥያት የተሰቀሉ፤ልክ እንደእየሱስ በሶስተኛው ቀን ከሞት የተነሱ፤ በመጨረሻም ወደ ሰማይ ያረጉ ፤ብዙዎቹ አዳኝ፤የአምላክ ልጅ፤ ጌታ የሚባሉ ከክርስቶስ ልደት ከ3000 አመት በፊት በተለያዩ አገሮች  የነበሩ አማልክት ሰዎች ነበሩ፡ እነዚህ ሁሉ ታሪኮች ቀና ብለን የምናያቸው የክዋክብት አካሄድና እውነታ ናቸው፡፡







ሁሉም ነገር የተጀመረው ክርስትናን እና የፓጋን ሀይማኖትን 

በአንድ ላይ አስማምቶ ለመግዛት ባሰበው በንጉስ ኮንስታንቲን 

ዘመን  320 አ.ም አካባቢ ነበር፡፡  ንጉስ ኮንታኒቲን እና በኒቂያ 

ጉባኤ ላይ ተሰብስበው የነበሩት አባቶች ክርስቶስ የተወለደው 

በታህሳስ ወር እንዳልሆነ ቢያውቁም በንጉሱ አስገዳጅነት እና 

ባለማወቅ ክርስቶስ የተወለደው ታህሳስ 25 አካባቢነው 

የሚለውን ሊቀበሉት ችለዋል በአሉ ልክ ለሳተርን አምላክ ይከበር 

እንደነበረውም የክርስቶስ ልደት ተብሎም መከበር ተጀመረ፡፡

ሰዎች በየአመቱ በአል ብለን የምናከብራቸውን በአላት ከየት መጡ ብለን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡አብዛኞቹ በአሎች የጥንት የሮማውያንና የባቢሎን የአምልኮ ስርአቶች የነበሩ ናቸውና፡፡ ሰላም ሁኑ፡፡

 

 

Comments

Popular posts from this blog

ድብቁ እውነት!! አዳም እና ሄዋን የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አልነበሩም!

የመሬት መንቀጥቀጡና መሰንጠቁ የወደቁት የታሰሩት መላእክት መውጣት! መጽሀፈ ሄኖክ የተናገረለት የአዛዝሄል መፈታት!