ድብቁ እውነት!! አዳም እና ሄዋን የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አልነበሩም!

 


አዳምና ሄዋን የመጀመሪያዎቹ ሰዎች እንደሆኑ የሰው ልጅም ከነሱ እነደመጣ መጽሀፍ ቅዱስ የሚነግረን እውነታና አለምም የሚያምንበት ነው፡፡ አዳም የመጀመሪያው ሰው አልነበረም የሚሉ  አስተሳሰብና እምነት እስከ 10ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በስፋት ይታመንበት ነበር ከ10ኛው ክፍለ ዘመን  በኋላ የዚህ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው በተለይ ክርስቲያኖች ይሳደዱና ይገደሉ ነበር፡፡ ሆኖም ብዙዎች ከ17ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ የነበሩ መጽሀፍ ቅዱስ ሊሂቃን እና የታሪክ ተመራማሪዎች አዳምና ሄዋን የመጀመሪያዎች ሰዎች እንደሆኑ አያምኑበትም፡፡ለዚህ ጥርጣሬ አዘል ጥያቄ መነሻ የሆነውም በ16ኟው ክ/ዘመን የነበሩ አውሮፓውያን አሳሾች አፍሪካና ደቡብ አሜሪካ ሄደው ያጋጠማቸው እነሱ ከሚያውቁት የተለየ አይነት ሰው በማየታቸው ነው፡፡የሰው ዘር ከአዳም የተገኝ ከሆነ እንዴት የተለያያ አይነት ዘር ሊገኘ ቻለ የሚለው ጥያቄ መጽሀፍ ቅዱስን እንደገና እንዲያጤኑት እና ከአዳምና ሄዋን በፊት ሰው ዘር ነበረ? የሚለውን ጥያቄ ለመጠየቅ አነሳስቷቸዋል፡፡  


ብዙዎቻችን የመጀመሪያዎች ሰዎች አዳምና ሄዋን እንደሆኑና የሰው ዘርም ከነሱ ነው የመጣው ብለን እናምናለን፡፡ነገር ግን ይሄን እምነት ሊያስቀሩ እና እንድንጠራጠር የሚያደርጉ የመጽሀፍ ቅዱስ ማስረጃዎችና አመክንዮች አሉ በዚህ ጽሁፍ እነዚህን እውነቱን የሚያስረዱ የመጽሀፍ ቅዱስ ማስረጃዎችና አመክንዮችን በትንሹ እናቀርባለን፡፡

የመጽሀፍ ቅዱስ የዘፍጥረት ታሪክ መነሻ ነው የሚባልለት እና ከመዛግብቶች ሁሉ ቀደምት የሆነው እና እውነታው በቤተክርስቲያን እንዳይታወቅ የተከለከለው እውነተኛው የሰው ዘር አመጣጥን የሚያትተው የድንጋይ ላይ ጽሁፍ የፍጥረት ታሪክ በላብራቶሪ ሰውን ዘር በወቅቱ የነበረው ኤሊያን ሬፕታሊያን  ፈጣሪ የኤደን ገነት ጌታ የነበረው  ኤንሊ፤መጽሀፍ ቅዱስ ያህዌ ይለዋል ፡ሴጣን ፤አርኮን ፣የውሸት አምላክ እንዴት ከሰው ልጅ ዲኤንኤ በመውሰድ እና በማዳቀል አዳምን ለባርነት እንደፈጠረው የሚያትተው ታሪክ አስደናቂ ነው፡፡


አዳም የመጀመሪያው የሰው ፍጥረት እንዳልሆነ ጥያቄ የሚያስነሳ የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ የአቤልና የቃየል ታሪክ ነው፡፡ በዘፍጥረት ም4.፡ቁ1 እንዲህ ይላል አዳምም ሚስቱን ሄዋንን አወቃት አቤልና ቃየንንም ወለዱ በዚያ ጊዜ  የአዳምና ሄዋን ልጆች አቤልና ቃየል ብቻ ነበሩ አቤልም በቅናት ተነሳስቶ ወንድሙን አቤልን ገደለው ፈጣሪም በወንድሙ አቤል ላይ ላደረገው ክፋት ረገመው ቃየንም እነዲህ አለ ሀጢያቴ ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት እነሆ ዛሬ ከምድር ፊት አሳደድከኝ ከፊትህም እሰወራለሁ በምድርም ተቅበዝባዠና ኮብላይ እሆናለሁ የሚያገኘኘም ሁሉ ይገድለኟል፡፡እግዚያብሄርም እሱን አለው እንግዲህ ቃየንን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልለታል እግዚያብሄርም ቃየልን የሚያገኘው ሁሉ እንዳይገለው ምልክት አደረገለት፡፡ ቃየንም ከእግዚያብሄር ፊት ወጣ ከኤደንም ወደ ምስራቅ በኖድ ምድር ተቀመጠ ቃየን ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ሄኖህንም ወለደች ከተማም ሰራ የከተማየቱንም ስም በልጁ ስም ሄኖህ አላት፡


እዚህ ጋር ነው እንግዲህ አወዛጋቢው ነገር ሚመጣው ከላይ እንዳየነው የመጀመሪያው ጥያቄ የሚያስነሳው አንዱ በወቅቱ የነበሩት ሰዎች ሶስት ብቻ ነበሩ  አዳም ሄዋን እና ቃየን ታዲያ  ቃየን ይገሉኛል ብሎ የፈራቸው ሰዎች እነማናቸው? ቃየን ያገኝኝም ሁሉ የገድለኛል ሲል ከአዳምና ሄዋን ውጨ ሌላ ሰው ካልነበረ አቤልንም ከገደለው ታዲያ ማንነው ይገድሉኛል ያላቸው፡፡ እግዚያብሄርም ቃየልን የሚያገኘው ሁሉ እንዳይገለው ምልክት አደረገለት ሲል የሚገሉት ሰዎች መኖራቸውን ያውቃል ማለት ነው?


እዚያው ምእራፍ ላይ ደግሞ በወቅቱ የነበሩት ሰዎች ሶስት ሰዎች  አዳም ሄዋን እና ቃየን ብቻ ከነበሩ ታዲያ ቃየን ሚስቱን ከየት አገኛት? ወይስ ሌላ ሰው በምድር ላይ ነበር ? ሌላው ጥያቄ የሚያስነሳው ነገር ደግሞ እዚያው ምእራፍ ላይ ከተማም ሰራ የከተማየቱንም ስም በልጁ ስም ሄኖህ አላት ፣እንዴት ነው ቃየን ብቻውን ከተማ የሚያክል ነገር ሊሰራ የሚችለው? ደግሞም  ሰዎች አልነበሩም ከተባለስ ለማንስ ነው ከተማውን የሚሰራው


እነዚህን ታሪኮች ለሚያነብ ሰው አንዳች የሚምምታታ ነገር እንዳለ ፣አዳምና ሄዋን ከመፈጠራቸው በፊት ሌሎች ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ? የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡ ሌሎችንም አዳም የመጀመሪያው ሰው እንዳልነበረ የሚያረጋግጡ ተመሳሳይ ጥቅሶችን ማቅረብ ይቻላል፡፡

በቤተክርስቲያን እንደሚታመንበትና እና ከመዛግብቶች እንደምናነበው አዳም ከተፈጠረ 6500 አመት እንደሆነ የሚታወቅ ነው ፡፡ሆኖም ከአዳም በፊት የሰው ልጅ ስልጣኔ እንደነበረ የሚያስረዱ በቆፋሮና በአንትሮፖሎጂ ጥናት የተገኙ ብዙ ፍራሾች እና የሰው አካል ቅሪቶች ተገኝተዋል ለምሳሌ ብንጠቅስ፣--

ዌስት ባንክ ኢያሪኮ የሚገኘው ቴተል አል ሱልጣን  ኢያሪኮ ፍርስራሽ ቅሪት 11000 አመት እድሜ ያለው ሲሆን የመጀመሪያው የሰው ልጅ የሰፈረበት እንደሆነ ይገመታል፤



ቱርክ የሚገኘው ጎባክሌ ታፔ እንዲሁ 11000 አመት ያስቆጠረ የቤተመቅደስ ቅሪት ይገኛል፡


አሌፖ ሶሪያ ቴል ካርሜል የሚባል ቦታ  12000 ኣመት ያስቆጠረ የሰው አካል ቅሪቶች ፣ ቁሳቁሶች እና ፍራሾች ተገኝተዋል፤


ሞንቲግናንች ፈረንሳይ 17000 ኣመት ያስቆጠረ የዋሻ ውስጥ ስእል አለ፤ እነዚህንና ሌሎች ብዙ ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡


የመጽሀፍ ቅዱስ የዘፍጥረት ታሪክ መነሻ የሆነው የሚባልለት እና ከመዛግብቶች ሁሉ ቀደምት የሆነው እና እውነታው በቤተክርስቲያን እንዳይታወቅ የተከለከለው እውነተኛው የሰው ዘርን አመጣጥ የሚያትተው የድንጋይ ላይ ጽሁፍ፣ የፍጥረት ታሪክ በላብራቶሪ የሰውን ዘር በወቅቱ የነበረው ኤሊያን ሬፕታሊያን  ፈጣሪ የኤደን ገነት ጌታ የነበረው  ኤንሊ፤መጽሀፍ ቅዱስ ያህዌ ይለዋል ፡ ሴጣን ፤አርኮን ፣የውሸት አምላክ እንዴት ከሰው ልጅ ዲኤንኤ በመውሰድ እና በማዳቀል አዳምን ለባርነት እንደፈጠረው የሚያትተውን ታሪክ ልንገራችሁ፡፡


  

በ1849 አንድ የእንግሊዝ አርኪዮሎጂስት ሱሜሪያ ኢራቅ ውስጥ 14 ታብሌት የድንይ ላይ ጽሁፍ ያገኛል፡፡ እንዚህ የድንጋይ ላይ ጽሁፎች ከክርስቶስ ልደት በፊት 2400 አመተ አለም የነበሩ የመጀመሪያዎቹ የድንጋይ ላይ ጽሁፎች ናቸው ፡፡የድንጋይ ጽሁፎቹን ከሌሎቹ ጥንታዊ ጽሁፎች ለየት የሚያደርጋቸው ስለ ፍጥረት የሚያነሱት ታሪክ ነው የዘፍጥረት ታሪክ፤አዳምና ሄዋን ፣ የገነት ዛፍ ታሪኮች እኛ ከምናውቀው በተለየ መልኩ የቀረበ መሆኑ ነው ይህም ይሄ ከ5500 አመት በፊት የተቀረጸ የድንጋይ ላይ መዛግብት በገነት ነበረው የፍጥረት ታሪክ  ከሌላ አለም/ፕላኔት የመጡ ፍጥረታት/አማልክት ታሪክ እንደሆነ ያትትና እነሱም ለምን እንደመጡ? ምን ፈልገው እአንደመጡ? እንዴት እንደመጡ? አስደናቂ መረጃ ይሰጣል፡፡



የሱሜሪያን መዛግብት ላይ እንደደሰፈረው ከ450 ሺ አመት በፊት እነዚህ ፈጣሪ፣አማልክት፣ ኤሊያን የሚባሉት ከሌላ ፕላኔት ወደዚህ ምድር ሲመጡ ምድር ጫካና  በውስጧም ልዩ ልዩ አውሬዎች እና ቀደምት የሰው ልጆች ይኖር ነበር ፡፡ እነዚህ ከሰማይ የመጡትን ፈጣሪዎች ወይም ኤሊያን አናኪ ይባላሉ ትርጉሙም ከሰማይ ወደ ምድር የመጡ ማለትነው አኑናኪዎች ከምድር በብዙ ርቀት ከሚገኝ ኒብሩ ከሚባል ፕላኔት ነው የመጡት፡፡ኒብሩ በየ3600 አመት ወደ ምድር ኦርቢት ይገባል፡፡ 

ብሩ ከምድር ብዙ እጥፍ የሚበልጥ እና ፕላኔቱ ባለው አይረን ኦክሳይድ ምክንያት ፕላኔቱ ላይ ያሉት ወንዞችና ሀይቆቹ  ቀይ ናቸው፡፡  የድንጋይ ላይ መዛግብቱ እንደሚሉት የኒብሩ የከባቢ የአየር ጸባይ በወቅቱ እየተመረዘና በፕላኔቱ ላይ የነበሩ ፍጥረታት መኖር ከማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ ያትታል ታዲያ የፕላኔቱን  የከባቢ የአየር ንብረት እንደገና ለመመለስ አኑናኪዎች አንድ ማእድን በጣም ያስፈልጋቸው ነበር ያማዕድንም ወርቅ ነበር ፡፡በእርግጥ ወርቅ የከባቢ የአየር ንብረትን እንደሚያሻሽል በሳይንስም የተረጋገጠ ነው ፡፡የራዲዬሽን ጨረራንም ስለሚከላከል ናሳ የስፔስ ጣቢያዎቹን በወርቅ ይለብጧቸዋል፡፡

አኑናኪዎች ወርቅ ለማውጣት ኤንኪ በሚባል መሪያቸው በመመራት የፐርሺያ ገልፍ አካባቢ በመምጣት ሰፍረው የወርቅ ማውጫ ጣቢያ መስርተዋል  የወርቅ ማውጫው ጣቢያ ኤርዱግ ይሉታል ምደራዊ ጣቢያ 1 እንደማለት ነው ፡፡ እነዚህ ጎብኚዎች ሲመጡ ታዲያ ብቻቸውን አልመጡም ኢጂጂ የሚባሉ እንደባሪያ የሚያሰሯቸው ከሌላ ፕላኔት የሌላ ዘር ፍጥረታትን አብረው ይዘው ነበር የመጡት፡፡ኢጂጂ ዝቅተኛ አናሳ ማለት ሲሆን ለአኑናኪዎች የወርቅ ማእድን የማውጣት ስራ ይሰሩላቸው ነበር ፡፡ ከብዙ መቶ አመታት በኋላ ኢጂጂዎች በአኑናኪዎች ላይ አመጹ፡፡ ኢጂጂዎች በማመጻቸው በአኑናኪዎች እና በኢጂጂዎች መካከል ጦርነት ተደረገ በጦርነቱም ኢጂጂዎች ሙሉ ለሙሉ ጠፉ፡፡ አኑናኪዎች በዚህ ምክኒያት በወርቅ ማውጯው ላይ የሚሰራላቸው አጡ በመሆኑም የአኑናኪዎች መሪ አኑ ልጁን ኤንኪን ጄኔትካሊ በማዳቀል አዲስ በወርቅ ማውጫው የሚሰራ አዲስ ፍጥረት እንዲፈጥር አዘዘው፡፡ አኑናኪዎች ሊሰሩት ያሰቡት አዲሱ ፍጥረት ብልሀትና ጥበብ ያለው እንዲሆን ነገር ግን ለከኑናኪዎች እነደ ባሪያ የሚገዛ መሆን እንዳለበት ወሰኑ፡፡ከብዙ ሙከራና የተለያዩ ፍጥረት እና ጃይንቶች የመሰሉ ከፈጠሩ በኋላ መጨረሻ ላይ ምድር ላይ ከነበረ ያልሰለጠነ ሰው እና የኤሊያን አኑናኪ ዘርን በመደባለቅ የሰውን ልጅ ለመፍጠር በቁ፡፡ የድንጋይ ላይ መዛግብቱ የመጀመሪያውን የተፈጠረ ሰው አዳሙ ይለዋል፡፡በእብራይስጥ አዳም ማለት ሲሆን ትርጉሙም ሰው ማለት ነው፡፡ 


አኑናኪዎች አዲሱን ሰው ሜሶፖታሚያና አካባቢው የሚገኙ የወርቅ ማውጨያዎች ውስጥ እንዲሰሩ አደረጓቸው፡፡ አዲሱ ፍጥረት አኑናኪዎችን ማምለክና ለነሱ መስራት ጀመረ፡፡ መዛግብቱ ላይ የተሳሉት ስእሎችና ጽሁፎች እንደሚያሳዩት እነዚህ አኑናኪዎች ከሰው ልጅ ይልቅ በጣም የገዘፉ፣ ጠንካራና ረጃጅም እጅግም ጥበበኞች ነበሩ፡፡ መዛግብቶቹ እንደሚገልጹት በአኑናኪ የተፈጠረው አዲሱ ፍጥረት ከግዜ በኋላ ቀስ በቀስ ከአኑናኪዎች ቋንቋን፤ ስልጣኔን፣ ማህበራዊ መስተጋብርን፤ ቤትና መሳሪያዎችን መስራትን ቴክኒዮሎጂዎችን ተማሩ፡፡ 


ከግዜ በኋላ የሰውን ልጅ ጄኔቲካሊ ኢንጂነርድ አርጎ በሰራው ኤንሊና የሰው ልጅ ባሪያ ሆኖ መቅረት አለበት በሚለው በወንድሙ ኤንኪ መካከል ጠብ ተነሳ፡፡ ይሄ ታሪክ ዘፍጥረት ላይ ኤንኪ የእባቡ ምሳሌ ሆኖ የሰው ልጅ ባሪያ ሆኖ መቅረት የለበትም እውቀት ያስፈልገዋል የሚለው ሲሆን ይሆዋ ደግሞ እውቀትን ካወቃችሁ ሞትን ትሞታላችሁ በሚለው የሚገለጽ ነው፡፡  

በየ3600 አመት ፕላኔት ኒብሩ ወደ ምድር ኦርቢት እንደምትገባና በምድር ላይ ጥፋት እንደምታመጣ ኒብሩዎች ያውቁ ነበር ኒብሩ አጥፊው ፕላኔት በመባልም ይታወቃል፡፡ መዛግብቱ ላይ እንደሰፈረው ኒብሩ ወደ ምድር ስትቀርብ ጥፋቶች ሁሉ ሱናሚ፤የመሬት መንቀጥቀጥ፤እሳተ ጎመራ እና ሌሎች መቅሰፍቶች ምድርን ያስጨንቋት ነበር በመጨረሻም የውሀ መጥለቅለቅ በምድር ላይ ተከሰተ በዚህ ወቅት ኤንሊ የሰው ልጆችን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት አጋጣሚውን እንደ ጥሩ እድል ነበር ያየው ፡፡ በወቅቱ ኤንሊ ወደ ኒብሩ ቢመለስም ሌሎች አኑናኪዎች ምድር ላይ ቀርተዋል፡፡በነበራቸውም የሰማይ መንኮራኩር ምድርን ከላይ ሆነው ጥፋቷን ይመለከቱ ነበር፡፡ ይሄን ጥፋት ቀድሞ ያየው የሰው ልጆች ወዳጅ የነበረው ኤንኪ ለሰው ልጆች በማዘን ጥቂት የተመረጡ ሰዎችን መርከብ እንዲሰሩ አዘዛቸው ከነዚህ ሰዎች መካከል ዛዮሱድራ(ኖህ ከነቤተሰቦቹ)እንዲተርፉ አድርጓል፡፡ ይሄ  የጥፋት ውሀ ታሪክ በአለም ላይ ባሉ ጥንታዊ ታሪኮች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ተጽፎ ይገኛል፡፡

እንግዲህ የዚህ አስደናቂ ታሪክ ጭብጡና በሚስጥር እንዲያዝ የተደረገበት ምክኒያት ምንድን ነው? በመጽሀፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ያለው አምላክ ያህዌ ከአኑናኪ የመጣ ፈጣሪ የሰውን ልጅ ለባርነት የፈጠረ መሆኑን ሚስጥሩ እንዳይወጣ ስለሚፈለግ ፣ የሱ አገዛዝ አሁንም በሀይማኖቶች ውስጥ አወቁትም አላወቁትም እንደቀጠለ ፍንጭ ስለሚሰጥ፣ እየሱስም ስለሱ ይናገር እንደነበረ፣ የሀይማኖትንም መሰረት ስለሚያናጋ ሰፊ ሚስጥር ያለው በመሆኑ ነው ሰላም ሁኑ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የመሬት መንቀጥቀጡና መሰንጠቁ የወደቁት የታሰሩት መላእክት መውጣት! መጽሀፈ ሄኖክ የተናገረለት የአዛዝሄል መፈታት!

ገናን (ክሪስማስን) Christmas ማክበር አስፈሪ ነው!እውነቱ ምንድን ነው!