የመሬት መንቀጥቀጡና መሰንጠቁ የወደቁት የታሰሩት መላእክት መውጣት! መጽሀፈ ሄኖክ የተናገረለት የአዛዝሄል መፈታት!
መጽሀፈ
ሄኖክ ም2 ከቁጥር 1 ጀምሮ እንዲህ ይላል በነዚያ ወራት መልከ መልካሞችና ደመ ግቡ ልጆች ተወለዱላቸው በደብር ቅዱስ ያሉ ደቂቀ
ሴትም እነሱን አይተው ወደዷቸው እርስበርሳቸውም ኑ ለኛ ከቃየል ልጆች ሴቶችን እንምረጥ ለኛ ልጆችን እንውለድ አሉ አርዲስ የሚባል
ቦታም ወረዱ ከነሳቸውም ሚስት አገቡ ሁሉም የየራሱን አንዳአንዲቱን መረጠ እነሱም ጸንሰው ረጃጅም አርበኞች ልጆችን ወለዱ ቁመታቸውም
ሶስት ሶስት ሺ ክንድ ነው ይላል፡፡ ከነሱም የተወለዱት ልጀች በምድር ላይ ከባድ ግፍን እንደሰሩ የምድር ጩህትም እስከ ሰማይ መድረሱና
በዚህም ምክኒያት እግዚያብሄር ሊያጠፋቸው እንደተነሳ ሄኖክ ዘርዝሮ ይነግረናል፡፡
ከዚያም
ወረድ ብሎ ሄኖክ ምእራፍ 3 ላይ አዛዝሄል የታሰረበትን ቦታ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡፡ ዳግመኟም እግዚያብሄር ሩፋኤልን አዛዝሄልን
እጅ እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ አግዘው በዱዳኤል ያለች ምድረበ ዳዋንም ክፈታት እሱንም በዚያ በጨለማ ውስጥ ጣለው፡፡
አዛዝሄልና
የወደቁት መላእክት ታስረው የተጋዙበት ይሄ ዱዳኤል የተባለ ቦታ የት ነው የሚለው ጥዯቄ ብዙ መላምቶች የተሰጡበት ነው ከባቢሎን
እስከ ሳህራ በረሀ ከበረዶአማው አርክቲክ እስከ ጥንታዊጧ ከተማ እየሩሳሌም ብሎም ፍልስጤም ብዙ ይባላል፡፡ አዛዝሄልና የወደቁት
መላእክት እዚህ ምድር ላይ ኢትዮጵያ ውስጠ አፋር ክልል ዳሎል እርታሌ ውስጥ እንደሆነ አሁን የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅና መሰንጠቅ
በመጨረሻው ዘመን የአዛዝሄል መፈታት አንቅስቃሴ እንደሆነ አስደናቂ እውነታዎችን አስገራሚ መረጃዎችን አቀርብላችኋለሁ ተከታተሉኝ፡።
ዱዳኤል
የት እንደሚገኝ ከስሙ ጀምሮ ያሉ ማስረጃዎችን እንይ ዱዳኤል የሚባለው
ቦታ ቅድም እንደጠቀስኩት በምድር ላይ ብዙ ቦታዎች ላይ እንዳለ መላምት ቢያስቀምጡም መንፈሳዊ አጥኚዎች ግን አሁን ያለው የአዛዝሄል
እና የወደቁት መላእክት መታሰሪያ ቦታ እዚሁ ኢትዮጵያ አፋር ውስጥ ዳሎል ኤርታሌ ነው ይላሉ፡፡
ሄኖክ
ምእራፍ 3 ላይ ያለውን ጥቅስ ስናይ ዳግመኟም እግዚያብሄር ሩፋኤልን አዛዝሄልን እጅ እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ አግዘው በዱዳኤል
ያለች ምድረበ ዳዋንም ክፈታት እሱንም በዚያ በጨለማ ውስጥ ጣለው፡፡ ዱዳኤል በግዜ ርቀት ዳሎል የሚለውን ስም መያዙ ይጠቀሳሉ፡፡ዳሎል
የሚለው ቃል ዱዳኤል ከሚለው ቃል ጋር በአለም ላይ ተመሳሳይ በርሀ የሆነ ቦታ ያለው ስም አልተገኘም፡፡ ዱዳኤል የሚለው ቃል በእብራይስጥ
የእሳት ቦታ ታላቅ በርሀ ማለት ነው፡፡ ስሙ ተመሳሰይ መሆኑ አስገራሚ ነው ዳሎል በርሀ ዱዳኤል ነው ይላሉ፡፡ በአለም ላይ እንደ ዳሎል ከፍተኛ ሙቀት ያለበትና የእሳት ባህር የሆነ ቦታ
የት ይገኛል፡፡
አንዳንድ አጥኚዎች ሲናገሩ ዱዳኤል ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ ቦታ ነው ይላሉ ይህ መረጃ በጥንታዊ መጽሀፍት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በታዋቂው ዊኪፒዲያ ላይ መረጃው ተቀምጦ እናገኘዋለን፡፡
ዱዳኤል ከየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ ቦታ
ከሆነ አፋር ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ ነው የምትገኝው ማለት ነው ለዚህ ማስረጃ የሳባ ንግስት ከምስራቅ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች የሚለው
አንዱ ሲሆን፡፡ሌላው ሰብአ ሰገል። የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ ይላል። ሰባአ ሰገል ኢትዮፕያውያን እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ዱዳኤል ከኢየሩሳሌም
በስተምስራቅ የሚገኝ ቦታ ነው እሱም ዳሎል ነው፡፡
ዳሎልና እርታሌ የምድራች ላይ ያለ ሌላ ፕላኔት የምድራችን ገሀነም ሲሉ አጥኘዎች ጽፈውለታል፡፡መንፈሳዊ አጥኚዎች የሳተ ጎመራ ያለበት አካባቢ እና በዚያ ዙሪያ ያሉ ቦታዎች በሽታ ፣ጦርነት እና አደጋ አያጣውም ይላሉ የዚህ ምክኒያቱን ሲያስቀምጡ እሳተ ጎመራዎችና እንደ እርታሌ ያሉ የእሳት ባህሮች ከወደቁት መላእክት ጋር አንዳች የሚያያይዛቸው ነገር ሊኖር እንደሚችል ይጠቅሳሉ።። ብዙ ግዜ ፊልሞች ላይ እሳተ ጎመራ ከድራጎን ጋር ተያይዞ ሲሰራ እናያለን፡፡ እሳት የሚተፋ ድራጎንም እንዳለ ይታወቃል፡፡ ምናልባት ይሄ ምስራቅ አፍሪካና መ/ምስራቅ የጦርነት እና የስቃይና፣ ቦታ የሆነው ከዚህ የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ዳሎል እርታሌ በብዛት የሚገኘው ሰልፈር ወይም እኛ ድኝ የምንለው ማእድን ከአጋንንት ጋር በእጅጉ እንደሚያያዝ እጅግ ብዙ ድኝ ያለበት ቦታ ከፍተኛ አጋንንቶች እንደሚኖሩበት ይናገራሉ፡፡
የገሀንም ሽታ ድኝ ድኝ ይላል የሴጣንም ዙፋን የተሰራው ከድኝ ነው የሚባል የአረቦች መጻጽፎችም አሉ፡፡ ዳሎል ከፍተኛ የሰልፈር ድኝ ክምችት መኖሩን ልብ ይበሉ፡፡ አዛዝሀሄነና የወደቁት መላእክት በዚህ ዘመን የመፈታታቸው እንቅስቃሴ ለምን ሆነ ቢሉ መንፈሳቸው ለታላቁ ጦርነት ሰዎችን ሊያስት ስለሆነ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ታላቅ መንፈሳዊ ጦርነት እንዲሁም ምድራዊ ጦርነት ተጀምሯል፡፡
አፋር
አዋሽ አካባቢ የተፈጠረው የመሬት መንቀጥቀጥና መሰንጠቅ አሁንም በአስፈሪ ሆኔታ ቀጥሏል፡፡ አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ ቦታዎች ላይ
በሬክተር ስኬል 4.9 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ መጠነኛ ጉዳት ተከስቷል፡፡ በዚያ የመሬት መንቀጥቀጡ ባመጣው ክስተት የታየው
የመሬት መሰንጥቅን ተከትሎ ምንነቱ ያልታወቀ የፈላ ውሀ ሳንጋቶ በሚባል ቀበሌ ውስጥ ከምድር ስር እየፈለቀ ይገኛል ይሄ ውሀ ምንነቱ
ስለማይታወቅ ገና ምርምር እየተደረገበት ይገኛል፡፡ውሀው ከቀን ውደቀን ብዛቱ እየጨመረ ከውስጡም ድምጽ እየተሰማ ነው፡፡
ይህን
ክስተት ሳይንቲስቶች ከምድር ጂኦሎጂካል ለውጥ ጋር አያይዘው የአፍሪካ
ለሁለት መሰንጠቅ በረዥም ግዜ ያስከትላል ሲሉ ሌሎች መንፈሳዊ ሰዎች ደግሞ
የትንቢቱ መፈጸም ግዜው መድረሱን የሚዯመለክት ነው ይላሉ ፡፡ ሀኪም አበበች ሽፈራውም ክስተቱ ከብዙ ዘመን ጀምሮ
የሚጠበቅ እንደሆነ በቅርቡ እንደሚከሰት ተናግረው ነበር፡፡ እርግጥ
ነው የመጨረሻው ዘመን ላይ እንዳለን በቂ ምልክቶች እየታዩ ነው ፡፡
ዩኒቨርሱ ከፍተኛ ለውጥ እያካሄደ
ነው የአፍሪካና የመካከለኘው ምስራቅ በመሬት መንቀጥቀጥና በሳተ ጎመራ የመሰንጠቁ ምክንያት ከታላቁ ጦርነት የመጣ እና የማይቀር ነገር ነው፡፡ የሚገርመው በኬሚስትሪ ከፍተኛ ተቀጣጣይ ፈንጂ ለመስራት የሚያገለግለው ኤለመንት
ስሙ ከአዛዝሄል ጋር የሚቀራረብ አዚዶ አዛይድ አዛይድ የሚባል ነው የሚገርም ነው፡፡
የጦር እቃን መስራትን ያስተማረው
ደግሞ አዝዝሄል ነው በሄኖክ መጽሀፍ እንዲህ ይላል… ምእራፍ
2 ቁጥር 16 አዛዛሄል ለሰዎች ሾተልና ሰይፍ መስራትን ጋሻ መሰጎድንም ጥሩር መስራትንም አስተማራቸው አዛዝሄልም ያደረገውን እይ በዚህ አለም ግፍን ሁሉ እንዳስተማረ በዚህ አለም
የተሰወሩትን ሁሉ በሰማያትም የተሰወሩት እንዳስተማረ እይ አሉት፡፡በዚህ
የመጨረሻው ዘመን የአዛዝሄል መንፈስ የኒውክሌር ጦርነት ለማስነሳት እንደሚመለስ ተብሎለታል ሰላም ሁኑ፡፡
.jpeg)

.jpeg)
.jpeg)
.jpeg)
Comments
Post a Comment