የመሬት መንቀጥቀጡና መሰንጠቁ የወደቁት የታሰሩት መላእክት መውጣት! መጽሀፈ ሄኖክ የተናገረለት የአዛዝሄል መፈታት!
መጽሀፈ ሄኖክ ም2 ከቁጥር 1 ጀምሮ እንዲህ ይላል በነዚያ ወራት መልከ መልካሞችና ደመ ግቡ ልጆች ተወለዱላቸው በደብር ቅዱስ ያሉ ደቂቀ ሴትም እነሱን አይተው ወደዷቸው እርስበርሳቸውም ኑ ለኛ ከቃየል ልጆች ሴቶችን እንምረጥ ለኛ ልጆችን እንውለድ አሉ አርዲስ የሚባል ቦታም ወረዱ ከነሳቸውም ሚስት አገቡ ሁሉም የየራሱን አንዳአንዲቱን መረጠ እነሱም ጸንሰው ረጃጅም አርበኞች ልጆችን ወለዱ ቁመታቸውም ሶስት ሶስት ሺ ክንድ ነው ይላል፡፡ ከነሱም የተወለዱት ልጀች በምድር ላይ ከባድ ግፍን እንደሰሩ የምድር ጩህትም እስከ ሰማይ መድረሱና በዚህም ምክኒያት እግዚያብሄር ሊያጠፋቸው እንደተነሳ ሄኖክ ዘርዝሮ ይነግረናል፡፡ ከዚያም ወረድ ብሎ ሄኖክ ምእራፍ 3 ላይ አዛዝሄል የታሰረበትን ቦታ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡፡ ዳግመኟም እግዚያብሄር ሩፋኤልን አዛዝሄልን እጅ እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ አግዘው በዱዳኤል ያለች ምድረበ ዳዋንም ክፈታት እሱንም በዚያ በጨለማ ውስጥ ጣለው፡፡ አዛዝሄልና የወደቁት መላእክት ታስረው የተጋዙበት ይሄ ዱዳኤል የተባለ ቦታ የት ነው የሚለው ጥ ዯ ቄ ብዙ መላምቶች የተሰጡበት ነው ከባቢሎን እስከ ሳህራ በረሀ ከበረዶአማው አርክቲክ እስከ ጥንታዊጧ ከተማ እየሩሳሌም ብሎም ፍልስጤም ብዙ ይባላል፡፡ አዛዝሄልና የወደቁት መላእክት እዚህ ምድር ላይ ኢትዮጵያ ውስጠ አፋር ክልል ዳሎል እርታሌ ውስጥ እንደሆነ አሁን የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅና መሰንጠቅ በመጨረሻው ዘመን የአዛዝሄል መፈታት አንቅስቃሴ እንደሆነ አስደናቂ እውነታዎችን አስገራሚ መረጃዎችን አቀርብላችኋለሁ ተከታተሉኝ፡። ዱዳኤል የት እንደሚገኝ ከስሙ ጀምሮ ያሉ ማስረጃዎችን እንይ ዱዳኤል የሚባለው ቦታ ቅድም እንደጠቀስኩት በምድር ላይ ብዙ ቦታዎች...