Posts

የመሬት መንቀጥቀጡና መሰንጠቁ የወደቁት የታሰሩት መላእክት መውጣት! መጽሀፈ ሄኖክ የተናገረለት የአዛዝሄል መፈታት!

Image
  መጽሀፈ ሄኖክ ም2 ከቁጥር 1 ጀምሮ እንዲህ ይላል በነዚያ ወራት መልከ መልካሞችና ደመ ግቡ ልጆች ተወለዱላቸው በደብር ቅዱስ ያሉ ደቂቀ ሴትም እነሱን አይተው ወደዷቸው እርስበርሳቸውም ኑ ለኛ ከቃየል ልጆች ሴቶችን እንምረጥ ለኛ ልጆችን እንውለድ አሉ አርዲስ የሚባል ቦታም ወረዱ ከነሳቸውም ሚስት አገቡ ሁሉም የየራሱን አንዳአንዲቱን መረጠ እነሱም ጸንሰው ረጃጅም አርበኞች ልጆችን ወለዱ ቁመታቸውም ሶስት ሶስት ሺ ክንድ ነው ይላል፡፡ ከነሱም የተወለዱት ልጀች በምድር ላይ ከባድ ግፍን እንደሰሩ የምድር ጩህትም እስከ ሰማይ መድረሱና በዚህም ምክኒያት እግዚያብሄር ሊያጠፋቸው እንደተነሳ ሄኖክ ዘርዝሮ ይነግረናል፡፡ ከዚያም ወረድ ብሎ ሄኖክ ምእራፍ 3 ላይ አዛዝሄል የታሰረበትን ቦታ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡፡ ዳግመኟም እግዚያብሄር ሩፋኤልን አዛዝሄልን እጅ እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ አግዘው በዱዳኤል ያለች ምድረበ ዳዋንም ክፈታት እሱንም በዚያ በጨለማ ውስጥ ጣለው፡፡ አዛዝሄልና የወደቁት መላእክት ታስረው የተጋዙበት ይሄ ዱዳኤል የተባለ ቦታ የት ነው የሚለው ጥ ዯ ቄ ብዙ መላምቶች የተሰጡበት ነው ከባቢሎን እስከ ሳህራ በረሀ ከበረዶአማው አርክቲክ እስከ ጥንታዊጧ ከተማ እየሩሳሌም ብሎም ፍልስጤም ብዙ ይባላል፡፡ አዛዝሄልና የወደቁት መላእክት እዚህ ምድር ላይ ኢትዮጵያ ውስጠ አፋር ክልል ዳሎል እርታሌ ውስጥ እንደሆነ አሁን የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅና መሰንጠቅ በመጨረሻው ዘመን የአዛዝሄል መፈታት አንቅስቃሴ እንደሆነ አስደናቂ እውነታዎችን አስገራሚ መረጃዎችን   አቀርብላችኋለሁ ተከታተሉኝ፡።   ዱዳኤል የት እንደሚገኝ ከስሙ ጀምሮ ያሉ ማስረጃዎችን እንይ   ዱዳኤል የሚባለው ቦታ ቅድም እንደጠቀስኩት በምድር ላይ ብዙ ቦታዎች...

ገናን (ክሪስማስን) Christmas ማክበር አስፈሪ ነው!እውነቱ ምንድን ነው!

Image
  በአለም ዙሪያ ያሉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ   ክርስቲያኖች ቀኑን በጉጉት በመጠበቅ ፣እርስ በርሳችሁ ስጦታ በመለዋወጥት ቀኑን ቅዱስ እንደሆነ በማሰብ የሚያከብሩት በአል ነው ገና፡፡ እውነታው ግን   የገና በዓል   ከየሱስ ክርስቶስ ልደት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ብላችሁስ፡፡ የገና በአል ከክርስቶስ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው እና   ወደ ክርስትና እምነት እንዲገባ በዘመናት ውስጥ የተደረገ ውሸት እንደሆነ ብነግራችሁስ፡፡ ታህሳስ 25 በጥንት ሮማውያንና ባቢሎናውያን የአምልኮ ስርአት የሚካሄድበትና ገናም ሴይጣናው አምልኮ ነው ብላችሁስ፡፡ በዚህች አጭር ጽሁፍ ጨለማውን በመግለጥ ስለ ገና ጥቂት እውነት እነግራችኋለሁ፡፡ አንደው ለመሆኑ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የገና ዛፍ ፤ የገና አባት፤ ስጦታ ተብሎ የሚዘጋጁ የተለያዩ ስጦታዎች፣ቁሳቁሶች ፣ጭፈራ ፣በግ ማረድ ፣.ሌሎችም ነገሮች ከክርስቶስ ልደት ጋር ምን ያገናኛቸዋል? ይሄን የሚጠይቅ አለ? እውነት የክርስቶስ ልደት ታህሳስ ወር እንደሆነ ማን ነው ያረጋገጠው ።መጽሀፍ ቅዱስ ላይ አንድም ቦታ ክርስቶስ   የተወለደው ታህሳስ ወር ነው አይልም፡፡ ክርስቶስ የተወለደበትን ቀን ማንም በእርግጠኘነት ሊናገር አይችልም፡፡ ምክንያቱም እውነታው ሌላ ስለሆነ፡፡  እስከ 16ኟው ክፍለ ዘመን በአብዛኞቹ የአሜሪካን ግዛቶች የገና በአል እንዳይከበር የተከለከለ ነበር   1647 በእንግሊዝ ፓርላማ የገና በአል እንዳይከበር የተከለከለ እና የሚያስቀጣ እንደነበር ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡ ታዲያ የክርስቶስ የልደት በአል ነው ብሎ በታህሳስ ወር ማክበር ከየት የመጣ ነው? እውነታውስ ምንድን ነው? ለምንስ እውነቱን   ሊደብቁን ፈለጉ? ለዘመናትስ ሲያስ...

ድብቁ እውነት!! አዳም እና ሄዋን የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አልነበሩም!

Image
  አዳምና ሄዋን የመጀመሪያዎቹ ሰዎች እንደሆኑ የሰው ልጅም ከነሱ እነደመጣ መጽሀፍ ቅዱስ የሚነግረን እውነታና አለምም የሚያምንበት ነው፡፡ አዳም የመጀመሪያው ሰው አልነበረም የሚሉ   አስተሳሰብና እምነት እስከ 10ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በስፋት ይታመንበት ነበር ከ10ኛው ክፍለ ዘመን   በኋላ የዚህ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው በተለይ ክርስቲያኖች ይሳደዱና ይገደሉ ነበር፡፡ ሆኖም ብዙዎች ከ17ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ የነበሩ መጽሀፍ ቅዱስ ሊሂቃን እና የታሪክ ተመራማሪዎች አዳምና ሄዋን የመጀመሪያዎች ሰዎች እንደሆኑ አያምኑበትም፡፡ለዚህ ጥርጣሬ አዘል ጥያቄ መነሻ የሆነውም በ16ኟው ክ/ዘመን የነበሩ አውሮፓውያን አሳሾች አፍሪካና ደቡብ አሜሪካ ሄደው ያጋጠማቸው እነሱ ከሚያውቁት የተለየ አይነት ሰው በማየታቸው ነው፡፡የሰው ዘር ከአዳም የተገኝ ከሆነ እንዴት የተለያያ አይነት ዘር ሊገኘ ቻለ የሚለው ጥያቄ መጽሀፍ ቅዱስን እንደገና እንዲያጤኑት እና ከአዳምና ሄዋን በፊት ሰው ዘር ነበረ? የሚለውን ጥያቄ ለመጠየቅ አነሳስቷቸዋል፡፡   ብዙዎቻችን የመጀመሪያዎች ሰዎች አዳምና ሄዋን እንደሆኑና የሰው ዘርም ከነሱ ነው የመጣው ብለን እናምናለን፡፡ነገር ግን ይሄን እምነት ሊያስቀሩ እና እንድንጠራጠር የሚያደርጉ የመጽሀፍ ቅዱስ ማስረጃዎችና አመክንዮች አሉ በዚህ ጽሁፍ እነዚህን እውነቱን የሚያስረዱ የመጽሀፍ ቅዱስ ማስረጃዎችና አመክንዮችን በትንሹ እናቀርባለን፡፡ የመጽሀፍ ቅዱስ የዘፍጥረት ታሪክ መነሻ ነው የሚባልለት እና ከመዛግብቶች ሁሉ ቀደምት የሆነው እና እውነታው በቤተክርስቲያን እንዳይታወቅ የተከለከለው እውነተኛው የሰው ዘር አመጣጥን የሚያትተው የድንጋይ ላይ ጽሁፍ የፍጥረት ታሪክ በላብራቶሪ ሰውን ዘር በወቅቱ የነበረው ኤሊያን ሬፕታሊያን ...